Saturday, February 27, 2016

ከቶ እንዴት ልሽኝሽ

፨ ከቶ እንዴት ልሽኝሽ ፨
***************
*ሊርበኝ አይኖችሽ
*ሊናፍቀኝ ገላሽ
*ከቶ እንዴት ልሸኝሽ...
አልክድም አልዋሽም
ትላንት፣ዛሬም፣ነገም ወድሻለዉ
ግን ማጣቴት ጠላዉ
ማጣቴ ሊያሳጣኝ ሊያርቅሽ
መሆኑን ሳስብ እፈራለዉ
ዴዝዴሞና ዷዝዴሞና
እያልኩ እጣራለዉ
የከዋክብት ንግስት
ዉዷ ጨረቃዪ የት ነሽ እልሻለዉ
ዉዴ ልቤ ፈራ
እንዴት ልሁን ከቶ ለማን ላዉራ
ማሬ አልቻልኩም
ፀሎት ማድረስ ለጌታዪ
ተንበርክኬ ማረኝ ብዪ
እየመጣ ምስል ገፅሽ
ከለከለኝ እንዳልፀልይ ወደ አምላክሽ
ዉዴ ዛሬም እልሻለዉ
ወድሻለዉ ወድሻለዉ ...
ልበል እንጂ ወድሻለዉ
*ላጣሽ እንደሆነ
ጠንቅቄ አዉቃለዉ
ምናልባት ናፍቆቴን ቢያስታግስልኝ

ከከንፈርሽ እንቡጥ ትንሽ አጉርሺኝ 
አንጀቴ ቢቃጠል በፍቅርሽ እፉኝ 
ቢያስታግሰኝ ብዪ ከንፈርሽን አልኩኝ
አዉቃለዉ ትወጂኛለሽ
*ከንፈርሽ አይኖችሽ
ሁሉም ይናገራል አንቺ
ግን ዝምትን መርጠሻል
አልፈርድብሽ ከቶ
በማታዉቂዉ አለም
ቃል ኪዳን ገብተሻል
መሀላ ፈፅመሽ ቀለበት አርገሻል
የጣትሽ ቀለበት
ቃል ኪዳን ቢሆንም
ዉብ ጣትሽን እንጂ
ልብሽን አያስርም
ልብሽ እኔ ጋር ነዉ
እሱንም አዉቃለዉ
ግን ማጣቴን ሳስብ
ደግሜ ፈራለዉ
ደግሜ አለቅሳለዉ
አንዴ ግን ልሳምሽ
ከንፈርሽን ስጪኝ
ሁሌም እንዳረሳሽ
ትዝታ እንዲሆነኝ
በልቤ ፅላት ዉስጥ
ፍቀጂ እንዳኖረዉ
ትላንት ወድሻለዉ
ዛሬም ወድሻለዉ
ነገም ............
**
**
**
%% በእሙሹ %%

See More

No comments:

Post a Comment